1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድረክ መግለጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ

ሰኞ፣ የካቲት 19 2010

የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ መግለጫ አውጥቷል። አስራ ሶስት ነጥቦችን የያዘው የመድረክ መግለጫ በሀገሪቱ ይታያሉ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል። መፍትሄውንም ጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/2tMuz
Äthiopien Gebru Gebremariam Beyene Petros Merara Merara Gudina
ምስል picture alliance/AP Photo/M. Ayene

የመድረክ መግለጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በሀገሪቱ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ አውጥቷል። አስራ ሶስት ነጥቦችን ከያዘው የመድረክ መግለጫ በሀገሪቱ ይታያሉ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል። ከእነዚህም ውስጥ ህዝብ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ ሲንቀሳቀስ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ እንደሚወሰድበት የሚጠቅሰው ይገኝበታል።

በኢትዮጵያ ፍትሃዊ የሆነ ስርዓት አለመዘርጋቱን፣ በሀገሪቱ የፍትህ መዛባት እና ሙስና መንገሱን ይጠቅሳል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ስለ መግለጫው ይዘት የመድረክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የውጭ ግንኙነት ሃላፊን ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን አነጋግሯል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ