የመኢአድ ጋዜጣዊ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 2008ማስታወቂያ
የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ትናንት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ለተቃዉሞ አደበባባይ በወጡ ሠላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱትን የሐይል እርምጃ የግፍ ጭፍጨፋ በማለት አወገዘዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ሕገ-ወጥ በሚል ሽፋን የሠላማዊ ዜጎችን ቤት እያፈረሰ ነዋሪዎችን ማፈናቀሉን እንዲያቆምም ድርጅቱ ጠይቋል።የድርጅቱ ባለሥልጣናት በንባብ ባሰሙት ባለ-ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ካልተሟሉ ፓርቲያቸዉ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገል አስጠንቅቀዋል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ