1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመን የገቡ ኢትዮጵያዉን መከራ 

ዓርብ፣ ሚያዝያ 12 2010

የየመን መንግሥት፤የሁቲ አማፂን፤ ታጣቂዎች  እና ሰዉ አሸጋጋሪዎች በአፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚፈፅሙት ግፉ አለቅጥ መክፋቱን የመብት ተሟጋቾች እና ስደተኞቹ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2wPqO
Jemen Bilderstrecke Familie Ruzaiq | Flüchtlinge
ምስል Reuters/A. Zeyad

«ይቀጠቅጡናል፤አስገድዶ መድፈር ሁሉ ይፈፀምብናል፤ የስቃይ ኑሮ ነዉ።» ስደተኞቹ

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጓች ድርጅት ሁይማን ራትስ ዎች እንደዘገበዉ የኢትዮጵያ፤ የኤርትራ እና የሶማሊያ ስደተኞች የመን ዉስጥ በሚገኙ በሁሉም ኃይላት ይደፈራሉ፤ ይደበደባሉ፤ ይታሰራሉ ሲከፋም ይገደላሉ።እዚያዉ የመን የሚገኙ፤ ከመከራዉ ያመለጡ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ አሁንም ከየመን መዉጪያ ያጡ ኢትዮጵያዉን እንደሚሉት በዱላ ብዛት እጅ እግራቸዉ ተቆርጦ ፤ ዓይናቸዉ ጠፍቶ ወይም ሌላ አካላቸዉ ጎድሎ የሚሰቃዩ በርካታ ኢትዮጵያዉን አሉ።ዩሐንስ ገብr። እግዚአብሔር የኢትዮጵያዉያንኑ አስተያየት እንደሚከተለዉ አሰባስቦታል።

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ