የላጋርድ ጉብኝ በአዲስ አበባ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 7 2010ማስታወቂያ
እየተበራከተ ለመጣዉ አፍሪቃዊ ወጣት የሥራ እድል ለመፍጠር የአሐጉሪቱ ኤኮኖሚ በፍጥነት ማደግ እንደሚገባዉ የዓለም ገንዘብ ድርጅት (IMF) ዋና ሐላፊ ወይዘሮ ክርስቲን ላጋርድ መከሩ።ኢትዮጵያን ለሁለት ቀናት የጎበኙት ላጋርድ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአፍሪቃ ዲፕሎማቶች እንደነገሩት የአፍሪቃ የሕዝብ ቁጥር እና የምጣኔ ሐብቱ እድገት መመጣጠን አለበት።የኢትዮጵያ መንግሥትም ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ፈቃድ እና ትኩረት እንዲሰጥ ኃላፊዋ አሳስበዋል።ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ