የሊቢያ ቀዉስና መፍትሔዉ
ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2009ማስታወቂያ
የሊቢያን ቀዉስ ለማስወገድ በጋራ «እንጥራለን» የሚሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የአዉሮጳ ሕብረት፤ የአፍሪቃ ሕብረት እና የአረብ ሊግ ተወካዮች ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ተሰብስበዉ ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ፌደሪካ ሞጎሮኒ የመሩት ሥብሰባ የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላት ያደረጉት ሥምምነት ገቢራዊነትን ገምግሟል።ለገቢራዊነቱ ሥለሚያስፈልገዉ ድጋፍና ርዳታም መክሯል።አራትዮሽ ተብሎ የሚጠራዉ ስብስብ የመጀመሪያ ስብሰባዉን ባለፈዉ መጋቢት ካይሮ ዉስጥ ያደረገ ሲሆን ሰወስተኛዉን አዲስ አበባ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል።የቀድሞ የሊቢያ አማፂያን በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የጦር ድጋፍ የቀድሞዉን የሊቢያ ሥራዓት ካፈራረሱ ወዲሕ ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሐገር የሥራዓተ-አልበኞች መፈንጫ ሆናለች።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ