1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ

ረቡዕ፣ መስከረም 10 2010

ሂዩመን ራይትስ ዋች ስለ እሬቻው አደጋ ባወጣው ዘገባ መንግሥት ከቀደሙት ዓመታት በተለየ አምና በዓሉ በተከበረበት ቦታ ላይ በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ማሰማራቱን አስታውሶ የበዓሉን ሂደት ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ የአሳዛኙ አደጋ መንስኤ ሆኗል ብሏል።

https://p.dw.com/p/2kOdl
Äthiopien Anti-Regierungs-Protesten
ምስል REUTERS/T. Negeri

የሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ

ባለፈው ዓመት በቢሾፍቱው የኢሬቻ በዓል ላይ ለደረሰው አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠያቂ ነው ተባለ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ስለ እሬቻው አደጋ ባወጣው ዘገባ መንግሥት ከቀደሙት ዓመታት በተለየ አምና በዓሉ በተከበረበት ቦታ ላይ በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ማሰማራቱን አስታውሶ የበዓሉን ሂደት ለመቆጣጠር የወሰደው እርምጃ የአሳዛኙ አደጋ መንስኤ ሆኗል ብሏል።  መንግሥት በዘንድሮዉ በዓል ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ሂዩመን ራይትስ ዋች ጥሪ አቅርቧል። ስለ ዘገባው የድርጅቱን የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳዮች አጥኚ ፌሊክስ ሆርንን ያነጋገረው የቶሮንቶው ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ  ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
አክመል ነጋሽ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ