የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብ/ፈተና መተላለፍ
እሑድ፣ ግንቦት 28 2008ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ሳምንት 254,000 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መፈተን ነበረባቸው። ግን፣ ፈተናው ሾልኮ በመውጣቱ ፈተናው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ፈተናው አንድ ቀን ሲቀረው «ኮድ14» የሚባለው የእንግሊዝኛ ፈተና ከነመልሱ በማህበራዊ ድረገፅች በመሰራጨቱ መቋረጡን የትምህርት ሚንስቴር ገልጾዋል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብ/ፈተና መተላለፍ
ሚንስቴሩ ለዚሁ ድርጊት «ሞራል የጎደላቸው» ያላቸውን ሰዎች ተጠያቂ አድርጓል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊው ፈተና ከሰኔ 27 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 እንዲደረግ ተወስኖዋል። ስለዚሁ ብዙ ማነጋገር የያዘው የፈተና መሰረቅ ጉዳይ ውይይት አካሂደናል።
አርያም ተክሌ
እሸቴ በቀለ