የ 2018 ዓለም የእግር ኳስ ግጥምያ ተጀመረ
ሐሙስ፣ ሰኔ 7 2010ማስታወቂያ
በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 21ኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊ ት በሉዝህኒዝኪ ስታዲየም በሩስያና በሳዉዲ ዓረብያ ብሔራዊ ቡድኖች ግጥምያ ጀምሮአል። በመክፈቻው ጨዋታዉ ሩስያ 4 ለ 0 ሳውዲን አሸንፋለች። የሳዉዲ ዓረብያ ታዳጊ ሴቶች በመክፈቻዉ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ሰንደቃላማን ይዘዉ ወደ ስቴዲዮም መግባታቸዉ ከሳዉዲ አኳያ ሴቶች ተሳታፊነታቸዉ ያልተለመደ በመሆኑ ትኩረት የሳበ ሆንዋል። በየሩሲያ የዓለም ዋንጫ ላይ 32 ሀገራት ይጋጠማሉ። በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2018 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ በሩሲያ በሚገኙ 11 ከተሞች በተዘጋጀ 12 ስታዲየም እንደሚካሄድ ታዉቋል። ከዘንድሮ ዉድድር ምን ይጠበቃል የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የዓለም እግርኳስ አሸናፊነቱን አስጠብቆ ይቀጥል ይሆን፤ አዜብ ታደሰ የግጥምያዉን መጀመር በጉጉት ይጠብቅ ከነበረዉ ከዶይቼ ቬለ የቀድሞ የእስፖርት ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋ ነበር።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ