ዝክረ-ድሬስደን
ማክሰኞ፣ የካቲት 6 2004ማስታወቂያ
እ. ኤ. አ. 1945 ዓ.ም. ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል። ወርሀ-የካቲት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት በጥምሩ ሀይል ድል ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቢቀሩት ነው። በድሬስደን ከተማ ሰማይ ላይ የጥምሩ ሀይል የጦር ጀቶች እየተመላለሱ ነው። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከተማዋ ላይ ያወረዱት የቦንብ ናዳ ከተማዋን እንዳልነበረች ያደርጋታል። ከአውሮፕላኖቹ የሚወረወሩት ቦንቦች ግዝፈት አይጣል ነበር። የድሬስደን ነዋሪዎች ከተማቸው በ15 ደቂቃዎች ውስጥ በቦንብ ውርጅብኝ እንዳልነበረች ሆና ዶግ አመድ የሆነችበትን ያቺን ቀን ከግማሽ ምዕተ- ዓመታት በላይ ከዓመት ዓመት ሲዘክሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። በዛች መከረኛ ምሽት ከ20.000 በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከአመዱ ውስጥ ተቀብረው ቀርተዋል። መፍቀሬ ናዚ ቀኝ አክራሪዎች ዕለቱን ለቅስቀሳ በመጠቀም ወደዚችው ከተማ መጉረፉቸውን ግን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሂሩት መለሰ