ውይይት፦ የእስረኞች ፍቺ አንደምታ
እሑድ፣ ጥር 13 2010ማስታወቂያ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ባለፈው ሰኞ ጥር 7ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በእስር ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች በይቅርታ ይፈታሉ ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የይቅርታ ሂደት እስከሚቀጥለው ሁለት ወራት እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ ከሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለማቀዛቀዝ ወይም ምላሽ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። የመንግሥት እርምጃ፤ ትክክለኛዉ ምክንያት እና ዉጤቱ የዚህ ሳምንት ዉይይታችን ትኩረት ነዉ። ነጋሽ መሐመድ የመራውን ሙሉ ውይይት ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ነጋሽ መሐመድ