1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ

እሑድ፣ ጥቅምት 5 2010

ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየበረደ ዳግም የሚያንሰራራዉ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በዚህ ሳምንትም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል። በዚህ ወቅትም ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋልም። በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የድንበር አካባቢዎች ለሰዎች ሕይወት መጥፋትና ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት የሆነዉ ግጭትም እልባት አላገኘም።

https://p.dw.com/p/2loaa
Äthiopien Irreecha Feierlichkeiten
ምስል DW/Y. Gebregzihabher

ውይይት

ተመሳሳይ የድንበር ዉዝግብ በተነሳባቸዉ በአፋር እና አማራ፤ በቡርጂ እና ጉጂም ግጭቱ ያለዘላቂ መፍትሄ ተዳፍኗል። ግጭቶቹ ተባብሰዉ ወደከፋ ደረጃ ሳይደርሱ ሊከላከላቸዉ ይገባ ነበር በሚል ማዕከላዊዉ መንግሥት በሚተችበት በዚህ ወቅትም የሀገሪቱ ምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ስልጣን ለመልቀቅ ጠይቀዋል። እዚህም እዚያም የሚነሱ ግጭቶች እና መፈናቀሎችን የሚመለከቱ ሀገሪቱ ወዴት እየሄደች ነዉ በሚል ስጋታቸዉን ይገልጻሉ። በአንፃሩ ኢትዮጵያዉያን አብሮ የመኖርን ጥቅም ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ያወቁበት ወቅት በመሆኑ አያሰጋም የሚሉም አልጠፉም። በእርግጥ የሀገሪቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴት እያመራ ነዉ?  የመወያያ ርዕሳችን ነዉ። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ