1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦህዴድ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረበው ጥሪ

እሑድ፣ የካቲት 11 2010

ከሁለት ዓመታት በላይ የዘለቀ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያልተጠበቁ ለዉጦች እየታዩ ነው። የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት በሚል የፖለቲካ እስረኞች እና ጋዜጠኞች ከእስር የመልቀቁ ሂደት ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/2spTP
Äthiopische Flagge und Polizist
ምስል DW/J. Jeffrey

ኦህዴድ የህዝቡን ጥያቄ እየመለሰ ይሆን?

 በተለይም በኦሮሚያ ክልል ለሚታዩ የለውጥ እንቅስቃሴዎች የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ጀምሯል። ለሕዝብ ጥያቄዎች ጆሮ መስጠቱን የገለጸው ኦህዴድ በቅርቡ በሀገር ዉስጥም ሆነ ውጭ ከሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ጥሪዉን አቅርቧል። ጥሪዉን በአዎንታዊነት የተቀበሉለት እንዳሉ ሁሉ ጥያቄ እና ጥርጣሬያቸዉን የገለፁም አሉ።  ውይይቱን በድምፅ ይከታተሉት።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ