1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

እሑድ፣ ሰኔ 3 2010

ካለፉት ዓመታት አንስቶ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በመፍትሄነት የሚቀርበው የብሔራዊ መግባባት ጥያቄ አሁንም እየቀረበ ነው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

https://p.dw.com/p/2zBrr
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

በኢትዮጵያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሾሙ በኋላ ፣በሀገሪቱ ፈጣን ለውጦች መካሄዳቸው ቀጥሏል። በነዚህ ጊዜያት ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተቃዋሚዎች እና ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ያነሷቸው የነበሩ ጥያቄዎች በከፊል እየተመለሱ ነው። የፖለቲካ እስረኞችን እና ጋዜጠኞችን በመፍታት የተጀመረው ለውጥ በሽብር የታስሩ እና የተከሰሱ ከሀገር ውጭም የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በይቅርታ እስከ መልቀቅ ዘልቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል። ፈጣኑ እርምጃ በዚህ ሳምንትም ቀጥሎ መንግሥት የኢትዮጵያ እና የኤርትራን የድንበር ግጭት ለመፍታት የተደረሰበትን የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል። ትላልቅ እና መለስተኛ የመንግሥት ድርጅቶችን በከፊል ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ እቅድ እንዳለውም አስታውቋል። እነዚህ እና የመሳሰሉት ለውጦች በሀገሪቱ ብሔራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ መንገድ ጠራጊ እርምጃዎች ተደርገው ቢወሰዱም በራሳቸው ግን በቂ እንዳይደሉ ነው የሚነገረው። እናም ካለፉት ዓመታት አንስቶ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በመፍትሄነት የሚቀርበው የብሔራዊ መግባባት ጥያቄ አሁንም እየቀረበ ነው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባት እንዴት? የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል። እነርሱም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአጭሩ መድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ፣ ዶክተር ታደሰ ብሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም አቶ ፋንታሁን ብርሀኑ የመግባባት የአንድነት እና ሰላም ማህበር ሃላፊ ናቸው።

ኂሩት መለሰ