1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደአውሮጳ የሚገቡ ስደተኞች ጉዳይ ያስነሳው ክርክር

ሐሙስ፣ ሐምሌ 16 2007

የአውሮጳ ሀገራት አፍሪቃውያን ስደተኞች በብዛት ወደ አህጉራቸው የሚመጡበት ድርጊት ትልቅ ችግር እንደደቀነባቸው ከማስታወቅ አልቦዘኑም። ሀገራቱ ቁጥራቸው ከፍ እያለ የመጡትን እና አስተማማኝ ባልሆኑ ጀልባዎች በሜድትሬንያን ባህር በኩል እያደረጉ ወደ አህጉሩ የሚገቡትን ስደተኞች ተቀብለው የማስተናገድ አቅም

https://p.dw.com/p/1G3rn
Flüchtlinge im Mittelmeer (Symbolbild)
ምስል picture-alliance/dpa/Bundeswehr/Hptm Kleemann

[No title]

እንደሌላቸው ወይም አቅማቸው የተወሰነ ብቻ መሆኑን ሲገልጹ፣ አንዳንዶች ደግሞ በስደተኞች እንደተወረሩ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ነገሮች ተጋነዋል፣ ገሀዱ ሌላ ነው የሚሉ ድምፆችም ይሰማሉ። በግብረ ሠናዩ ድርጅት «ቴር ዴ ዞም እና በዓለም የምግብ ድርጅት ጥያቄ ወደ አውሮጳ ስለሚገቡት ስደተኞች እንቅስቃሴ ተከታትለው ያዘጋጁትን ጥናት ትናንት በበርሊን ይፋ ያደረጉት በጀርመን የኦዝናብሩግ የኒቨርሲቲ የባህል ግንኙነት ጥናት ተቋም ተመራማሪ ዮኽን ኦትመር አፍሪቃውያን በገፍ ወደ አውሮጳ እየመጡ ነው የሚለው አነጋገር ትክክል እንዳልሆነ አመልክተዋል። ስለጥናቱ ይዘት ሀይነር ኪዝል ያዘጋጀውን ዘገባ ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ሀይነር ኪዝል/ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ኂሩት መለሰ