1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፓሪሱ ስምምነት አወጣጥ ሂደት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2009

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ጉዳይ ስምምነት እንደምትወጣ ይፋ አድርገዋል። አሁን በዚሁ አቋማቸዉ መፅናታቸዉ በቡድን ሰባቱ የበለፀጉ ሃገራት ስብሰባ ላይም በድጋሚ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/2eeMy
Trump, Paris Abkommen, Climate Change, Karikatur, Elkin, Sergey Elkin

ከፓሪሱ-ስምምነት-አወጣጥ-ሂደት

 

 የቡድን ሰባት አባል ሃገራት የሆኑት ሌሎቹ ማለትም የካናዳ፣ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ ጃፓን እና ዩናይትድ ኪንግደም ማለትም ብሪታንያ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች የፓሪሱ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ቅነሳ የሚመለከተዉ ስምምነት ወደኋላ የማይመለስና ዳግም ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ስምምነት እወጣለሁ ብትልም እንዲህ ካለዉ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት የወጣጡ ሂደት ቀላል እና አጭር እንደማይሆን በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ተፈጥሮ ዲዛይን ፋኩልቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የዘርፉ ተመራማሪ፤ ለሆኑት ለዶክተር ጌታቸዉ አሰፋ አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋሽንግተን ከዚህ ስምምነት ራሷን ማግለል ምን ያስከትላል? የአወጣጧስ ተግባራዊነት ለሚሉት ተያያዥ ጥያቄዎች ማብራሪያ ከድምጽ ዘገባዉ ማድመጥ ይችላሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ