ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቀዉ የአየር ንብረት ለዉጥ
ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2008ማስታወቂያ
ወደከባቢ አየር ከፍተኛ የበካይ ጋዝ መጠን የሚለቁት ሃገራት የግል ብልፅግና እና የልማት እድገታቸዉ እንዳይደናቀፍ በመስጋት ሊወስዱት የሚገባዉ ርምጃ ላይ መወሰን የቻሉ አይመስልም። በካይ ጋዙ ባስከተለዉ የአየር ንብረት ለዉጥ መዘዝ የተጋለጡ ሃገራት ከበለፀጉት የኢንዱስትሪ ቱጃሮች የሚጠብቁት የገንዘብ ድጋፍ በፓሪሱ የአየር ንብረት ተመልካች ጉባኤም ዋነኛ አነጋጋሪ ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። አንድ ሀገር ወደከባቢ አየር በሚለቀዉ የበካይ ጋዝ መጠን ምን ያህል ገንዘብ ለዚህ መክፈል ይኖርበታል የሚለዉም አከራካሪ ነዉ። ኤኮኖሚ ባለሙያዎች ግን መፍትሄ ያሉትን በጋራ የበጎ አድራጎት የልማት ድርጅት ቢቋቋም እንደሚበጅ እየመከሩ ነዉ። የዕለቱ ከኤኮኖሚዉ ዓለም ይህን ይመለከታል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ