1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ጋር የተዘጋጀ ብሔራዊ ምክክር

ሰኞ፣ መጋቢት 5 2014

ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ ሃገራዊ ብሔራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ያዘጋጀው ጉባኤ ተጀመረ። የመድረኩ ተጠባባቂ ኘሬዚዳንት ኘሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንዳስታወቁት፤ ጉባኤው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ተቋም ጋር በመተባበር ነው።

https://p.dw.com/p/48S6P
Karte Äthiopien englisch

ብሔራዊ ምክክር

ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ ሃገራዊ ብሔራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ያዘጋጀው ጉባኤ ተጀመረ። የመድረኩ ተጠባባቂ ኘሬዚዳንት ኘሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንዳስታወቁት፤ ጉባኤው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ተቋም ጋር በመተባበር ነው። የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች መድረክ የቦርድ አባል ዶክተር ዩሐንስ ዘለቀ በበኩላቸው፤ የሌሎች ሃገሮችን ተሞክሮ በማውሳት በኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ለማካሄድ መታሰቡ በጎ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ የገለልተኝነት ጥያቄ እንደሚነሳበት ሂደቱም ግልፅ አይደለም በሚል የሚቀርበውን ቅሬታም ጉባኤው የሚዳሰስው ጉዳይ እንደሆነ ተመልክቷል።


ታሪኩ ኃይሉ


አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ