ከባሬስታነት እስከ ታዋቂ ተዋናይነት
እሑድ፣ የካቲት 4 2010በጎንደር እንብርት ፒያሳ ተወልዶ፤ የአንገበርን ዉኋ ጠጥቶ፤ ጃንተከል ዋርካ ዙርያ ተዝናንቶና ቦርቆ ያደገዉ፤ ተዋናይ ፋሲል ተካ በልጅነቱ ከሊስትሮነት ሎተሪ አዟሪነት ሥራን ጀመረ። በመለጠቅ በዝያዉ በከተማዋ ሲማቤት ቡና ቤት ዉስጥ በአስተናጋጅነት ተቀጥሮ ሲሰራም ለዛሬዉ የመድረክ ፈርጥነት መብቃቱን እሱ ብቻ ሳይሆን አድናቂዎቹ አብሮ አደጎቹ ይመሰክራሉ። በጎንደር ሲኒማ ቤት የጀመረዉ የመድረክ ተዉኔት ባሕርዳርን ይዞ በቀጣይ መዲና አዲስ አበባ ላይ በተለይ የቋራዉን ጀግና የአፄ ቴዮድሮስን ጀግንነት ገፀ ባሕሪና አልባሳቱን ተላብሶ ሲተዉን ተወዳጅነት እና ታዋቂነትን አትርፎለታል። ይኸዉ ድንቅ ትዉናዉ በሰሜን አሜሪካ ከ 25 ብላይ ግዛቶች ተዘዋዉሮ እንዲጎበኝ ድንቅ ትርዔቱን ለተመልካቹ እንዲያቀርብ በርከፍቶለታል። በሰሜን አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በመኃል አዉሮጳ ሐገራትም የተለያዩ ሐገራትን በተለይ ደግሞ መዲና ጀርመንን ተዘዋዉሮ ጎብኝቶአል። ተዋናይ ሱራፌል ተካ በጀርመን ቆይታዉ ዶይቼ ቬለን ለማግኘት እድል ባያገኝም ዛሬ ከሚገኝበት አዲስ አበባ ከሚተዉንበት ከመድረክ ጀርባ በሥልክ አግኝተን በእንግድነት ይዘነዋል።
የዛሬዉ የመድረክ ተዋናይ ሱራፌል ተካ በልጅነቱ የፊልምን ማየት ስለሚሻ ብቻ ሲኒማ ቤት ተቀጥሮ በብዛት ፊልምን ለማየት እንደበቃ እና ከተመለከተዉ ፊልም በኋላ የተማረከበትን የፊልም አክተር ገፀ-ባህሪን አስመስሎ መጫወት መጀመሩ ለዛሬዉ የትያትር መድረክ ትወና ጥርግያ እንደከፈተለት ይናገራል።
ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።
አዜብ ታደሰ