1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳዑዲ አረቢያ የሚወጡ ኢትዮጵያዉያን መከራ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2009

ኢትዮጵያዉኑ ብዙ ሳይንገላቱ ወደ ሐገራቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት አብክረዉ እየጣሩ መሆኑን ቢያስታዉቁም ተመለሾቹ የአዉሮፕላን ቲኬት እንኳን ለመግዛት እስከ አምስት ቀን ድረስ ለመመላለስ መገደዳቸዉን ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/2eeFt
Illegale aus Äthiopien in Saudi-Arabien
ምስል DW/Sileshi Sibiru

(Beri.Riyadh) Ethiopien returnees in Riyadh - MP3-Stereo

ከሪያድ ህገወጥ የተባሉ ኢትዮጵያዊያንን የማስወጣቱ ሂደት የምህረት ጊዜው እያለቀ በመጣ ቁጥር ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሮበታል፡፡ ሊመጣ የሚችለውን እስር እና እንግልት ለመቀበል ቆርጠው ከሳዑዲ ዓረቢያ አንወጣም ያሉት አብዛኞቹ ቀርተው ለመመለስ ፍቃደኛ ሆነው የተመዘገቡት እንኳን በአየር ትኬት ያለመኖርም ሆነ እሱን ተከትለው በተፈጠሩ የመስተንግዶ ማጣት እየተንገላቱ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡

በሌላም በኩል ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች አንድም እንኳን እንግልት እና ስቃይ ሳይደርስበት ወይንም ሳይደርስባት ሳዑዲን በጊዜ ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል  የኢትዮጵ መንግስት በፍጹም የሀላፊነት ስሜት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በኩል አስታውቋል ፡፡

በሪያድ ሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያዊያን ተመላሾች ምሬት እና ሮሮ ዛሬም የየ እለት ክስተት ሆኗል፡፡ በተለይ የሳዑዲ መንግስት ያወጣው የበጊዜ ውጡልኝ የምህረት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ከ 2 ሳምንት በታች እየቀረው መጓጓዣ እሄዳለሁ ብሎ በቆረጠው ዜጋ መጠን ያለመገኘቱ ብዙዎቹን ለመሬት ዳርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ መጀመሪያ ጀምሮ ተጨማሪ አይሮፕላኖችን በመመደብም ሆነ ተደጋጋሚ በረራዎችን በማድረግ የማጓጓዙን ተግባር እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም እስካሁን እውን የሆነ ነገር የለም የተሰጠው ምክንያት ደግሞ ከሳዑዲ በኩል ተጨማሪ አይሮፕላን ለማሳረፍ ፍቃድ አልተገኘም የሚል ነው፡፡  ያም ሆነ ይህ በርካታ እናቶች ከነ ጨቅላ ልጆቻቸው ጋር ትኬት ፍለጋ 3 እና አራት ቀናት በመመላለሳቸው መማረራቸውን ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵ መንግስት ግን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መስሪያ ቤት አማካኝነት ያወጣው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩን በስም ጠቅሶ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከሳዑዲ መሪዎች ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ለዜጎቻችን አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሌት ተቀን መድከማቸውን አትቷል፡፡

ከዚህም በላይ መግለጫው በርካታ ዲፕሎማቶች ትላልቅ ሀገራዊ ጉዳዮችን ለጊዜው አቁመው ከኤምባሲው እና ቆንስላው ውጭ ለኑሮ በማያመች በረሃማ ስፍራዎች ላይ ሆነው ወገኖቻችንን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማስወጣት እያገለገሉ እንደሚገኙ ይገልጻል፡፡

በሪያድ ያለው የእናቶች ምሬት  ግን ከመግለጫው ጋር እምብዛም አይጣጣምም፡፡ የሃምሳ በመቶ ቅናሽ ተደርጎበታል የሚባለው የአየር ቲኬት ዋጋም ቢሆን ከእውነታው የራቀ ነው ፡፡ ያለፉት ቅርብ አመታት የትኬት ታሪክ እንደሚያሳየው የደርሶ መልስ ትኬት እንኳን ከ1600 ብር በላይ ወጣባቸው ጊዚያቶች እጅግ ጥቂት ወራት ላይ ነው ፡፡ የአንድ ጉዞ ትኬት ከ1200 ሳዑዲ ሪያል ዘሎም አያውቅም ፡፡ የ1200 50 በመቶ ደግሞ 900 ሳዑዲ ሪያል ሊሆን አይችልም፡፡

የሳዑዲ መንግስት የስቀመጠው የውጡልኝ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ከ2 ሳምንት በታች ነው የቀረው፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ትላንት ለዶቸ ቨለ እንደ ገለጹት ከሳዑዲ ለመመለስ ከተመዘገቡት 60 ሺህ ያህል ኢትዮጵያዊያን ግማሽ ያህሉ ሀገር መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ