1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳውዲ የሚወጣ ገንዘብ

ማክሰኞ፣ ጥር 16 2009

የሳውዲ የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ በትዊተር ባሰራጨው መልዕክት ሳውዲ አረብያ ወደ ሀገርዋ በሚገባ እና በሚወጣ ገንዘብ ነጻ ዝውውር እንደምትጸና አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/2WJn8
Symbolbild Geldsegen Dollar
ምስል Fotolia/Sergey Galushko

Q&A mit Korri in Riyadh( Gvovernment says no fees to remittances) - MP3-Stereo

የሳውዲ አረብያ መንግሥት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገንዘብ ሲልኩ ቀረጥ እንዲጣልባቸው የቀረበለትን ሀሳብ ተግባራዊ እንደማያደርግ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታወቀ ። ሹራ የተባለው የዘውዳዊው ስርዓት አማካሪ ምክር ቤት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሚልኩት ገንዘብ ላይ 6 በመቶ ቀረጥ እንዲከፍሉ ባለፈው ዓመት ሀሳብ አቅርቦ ነበር ። ይሁንና የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባለፈው እሁድ በትዊተር ባሰራጨው መልዕክት ሳውዲ አረብያ ወደ ሀገርዋ በሚገባ እና በሚወጣ ገንዘብ ነጻ ዝውውር እንደምትጸና አስታውቋል ። በጉዳዩ ላይ የሪያዱን ወኪላችንን ስለሺ ሽብሩን ቀደም ሲል በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። 
ስለሺ ሽብሩ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ