1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሞያሌ ለተፈናቀሉት ወገኖች የገንዘብ ርዳታ

ረቡዕ፣ መጋቢት 12 2010

በኦሮሚያ ዉስጥ ከምትገኘዉ የሞያሌ ከተማ እና አካባቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን የገንዘብ ርዳታ በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ድርጅት አማካኝነት ከኢትዮጵያዉያን ተሰጠ። ርዳታዉን የሰጠዉ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዉያን መብት የሚባለዉ ድርጅት በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት በኩል 10 ሺህ ዶለር ለኬንያ ቀይ መስቀል መላኩን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/2ui5D
Äthiopien vertriebene Moyale-Bewohner in der Oromia-Region
ምስል privat

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዉያን መብት የሰጠው ርዳታ

 ድርጅቱ ለተፈናቀሉት ወገኖች ለጊዜዉ ፈጥኖ ለመድረስ የሰጠዉ ይህን የገንዘብ ርዳታ በኬንያ ገንዘብ ከአንድ ሚሊየን ሽልንግ በላይ እንደሚሆን ነዉ የተገለጸዉ። የገንዘብ ርዳታዉ ከትናንት በስተያ ለአሜሪካዉ ቀይ መስቀል መሰጡትን ያመለከቱት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ታማኝ በየነ ርዳታዉ ሊቀጥል እንደሚችልም አመልክተዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ