1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦቲዝምና የነርቭ ስርዓት ትስስር

Shewaye Legesseማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2016

https://p.dw.com/p/4f43X

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኦቲዝም ዘንድሮ በያዝነው ሚያዝያ ወር ሲታሰብ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ስለኦቲዝማ የአእምሮ እድገት ውሱንነት በየጊዜው ሲነገር እንሰማለን። ኦቲዝም የአንጎል እድገት ውስብስብ ችግሮች በቡድን የሚገለጹበት መሆኑን የሚያመለክቱ ማብራሪያዎች አሉ። በዚህ እክል ውስጥ ያሉ ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው የሚታወቁ ሲሆን ከአካባቢያቸው ተላምደውና ተዋህደው ለመኖር እንደሚያዳግታቸው ይገለጻል። የራሳቸው ዓለም አላቸው የሚባሉት የኦቲዝም ሰለባዎች በተግባብቦት ሂደት የሚያሳይዋቸው ሦስት ነገሮች እንዳሉ ነው ዶክተር ተሻገር የሚናገሩት። የቋንቋና ተግባቦት መገደብ፤ ትርጉም የሌለው እንቅስቃሴ እና ድምጽ ማውጣት የመሳሰሉ ያልተለመዱ ነገሮችን እንደሚያዘወትሩ አመልክተዋል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

Symbolbild Herzschlag Herz EKG Stethoskop
ምስል Fotolia/M&S Fotodesign

ጤና እና አካባቢ

በዚህ ዝግጅት በየሳምንቱ የጤና፣ የአካባቢ ተፈጥሮን እንዲሁም ኅብረተሰቡን የሚያሳስቡ፤ በልዩ ትኩረት ደግሞ ሴቶችን የሚመለከቱ ጥንቅሮች ይቀርባሉ። የባለሙያዎች ቃለመጠይቅ፣ ከአድማጮች ለሚቀርቡ ጤና ነክ ጥያቄዎች የህክምና ባለሙያዎች ማብራሪያ እና ምላሽ፣ እንዲሁም አርአያ የሚሆኑ ግለሰቦች የሕይወት ተሞክሮዎች ይስተናገዳሉ። አዘጋጅ ሸዋዬ ለገሠ