1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ኦህዴድ»፤ ሊቀመንበር መምረጡና አስተያየት   

ሐሙስ፣ የካቲት 15 2010

የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዲድ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ዶር አቢይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር  አድርጎ ሾመ። የኦህዲድ የሕዝብ አስተያየትና ፐብሊሲቲ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጎፊ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የዶክተር አብይ ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ምርጫ የተደረገ ሽግሽግ አይደለም።

https://p.dw.com/p/2tAJY
Äthiopien Abiy Ahmed OPDO
ምስል Abdulbasit Abdulsemed

2_OPDO statement & Reax_pro contra - MP3-Stereo

በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች ሽግሽጉ ምንም የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም ብለዋል። የኦህዲድ ማዕከላዊ ኮሚቴ  ዶር አቢይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር  አቶ ለማ መገርሳን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙ የተሰማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነበር። የኦህዲድ የሕዝብ አስተያየትና ፐብሊሲቲ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሳሁን ጎፊ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት ዶክተር አብይ አህመድ ለሊቀመንበርነት የተመረጡት በሙሉ ድምጽ ነዉ።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የተቃዋሚው የኦፌኮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዲሁም የኦፌኮ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሙላቱ ገመቹ  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» በምህጻሩ ስለ ዛሬው የኦህዴድ ውሳኔ ለዶቼቬለ በሰጠው አስተያየት «ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም ሲል ተችተዋል። 

የኦህዲዴ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ስላካሄደው ሹም ሽር ለዶቼቬለ አስተያየት ከሰጡት አንዱ  ጦማሪ አብዱል ባሲጥ አብዱል ሰመድ ነው።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሠ