1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እንቡጥ» ኢትዮ-ፈረንሳይ ግብረሰናይ ማኅበር

ሰኞ፣ ግንቦት 15 2008

በርካታ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎችን በመደገፉ የሚታወቀዉና በጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ,ም በፈረንሳዉያንና በፈረንሳይ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያዉያን የተመሠረተዉ «እንቡጥ» የግብረሠናይ ማኅበር 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በድምቀት አከበረ።

https://p.dw.com/p/1It6e
Frankreich Paris Champs-Elysees Avenue autrofreier Sonntag
ምስል Getty Images/AFP/L. Bonaventure

«እንቡጥ» የተሰኘዉ ይህ ማኅበር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ወላጆች ልጆችንና ቤተሰቦቻቸዉን በሞት ያጡ ችገረኛ ልጆችን የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን እንዲሁም የኪስ ገንዘብ በመስጠት ጭምር ትምርታቸዉን እንዲከታተሉ ሲረዳ ቆይቶአል። ማኅበሩ በተለይ አዲስ አበባ በሚገኘዉ ድል በር የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ታዳጊና ችገረኛ ተማሪዎችን ከፍተኛ የትምርት ተቋም እስኪደርሱ ድረስ ክትትል በማድረግ ትምህርታቸዉን ተከታትለዉ እስኪያጠናቅቁ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተነግሮአል። ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ማኅበሩ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ በከፍተኛ ድምቀት ባከበረበት ወቅት፤ በዚሁ ማኅበር ድጋፍ አግኝተዉ የሁለተኛና ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን አጠናቀዉ ለሥራ የሚበቁ በርካታ ተማሪዎች ማፍራቱ ተገልፆአል። በዚሁ ዝግጅት ላይ የተገኘችዉ የፓሪስዋ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልካልናለች።

ኃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ