ኤችአር 128 በአሜሪካ ምክር ቤት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010ማስታወቂያ
ባለፈው ዓመት ድምፅ ይሰጥበታል ተብሎ በነበረው በኤች አር128 ውስጥ ኢትዮጵያ እንድታሟላቸው ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል የእስረኞች መፈታት አንዱ ሲሆን ባለፉት ጥቂት ጊዚያት የኢትዮጵያ መንግሥት አንዳንድ እስረኞችን የፈታበት ዓይነቱ ርምጃ በዛሬው ድምፅ አሰጣጥ ላይ ተፅዕኖ ማሳረፍ መቻል አለመቻሉን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይታወቃል። የዋሽንግተኑ ወኪላች መክብብ ሸዋ እንዳለው፣ ለረቂቁ የውሳኔ ሀሳብ የእንደራሴዎቹን ድጋፍ ለማፈላለግ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚተቹ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን በሚገኘው የዩኤስ አሜሪካ ምክር ቤት ደጃፍ ሰልፍ ያደርጋሉ። ስለ ኤችአር 128 ድምፅ አሰጣጥ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን መክብብ ሸዋን አነጋግረነዋል።
መክብብ ሸዋ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ