1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጋድ በፍልሰት አስተዳደር

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ግንቦት 11 2008

ዛሬ የተጠናቀቀዉ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት «ኢጋድ» ጉባኤ ስደትን በሚመለከት ሕጋዊ ማዕቀፎች፣ እንዲሁም ፍልሰትን ለማስቆም አባል አገሮች ያላቸዉን ቁሳዊም ሆነ የገንዘብ አቅም በተመለከተ ተወያይቷል።

https://p.dw.com/p/1Iql2
Fahnen der IGAD-Mitgliedsländer
ምስል Yohannes G/Eziabhare

[No title]

በዚህም ከአባል አገራት የሚመነጩት ሕጋዊ ያለሆነ የሰዎች ዝውውር፣ የሰዎች እንቅስቃሴ እና ሕጋዊ ፍልሰትን በተመለከተም መረጃ መለዋወጥ ታስቦ እንደሆነም ተጠቅሷል። ስብሰባዉ ካሳካቸዉ ነገሮች ዉስጥም ስምንቱ የኢጋድ አባል አገሮች «national consultative mechanism on migration» በመባል የሚታወቀዉ የፍልሰት የመቆጣጠሪያ ማዕቀፍ አማካኝነት በብሔራዊ ደረጃ የፍልስት አስተዳደር ሥራ ላይ እንዲያዉሉ ማድረግ አንዱ መሆኑን የኢጋድ የፍልስት ጉዳዮች አስተባባር ካሮሊና ንጆኬ ለዶቼ ቬሌ ገልጸዋል። የአፍሪቃ ቀንድ ፍልሰትም ዓለም አቀፍ ትኩረት እንደሳበ የሚናገሩት አስተባባሪዋ የካርቱም ስምምነት፣ የቫሌታ ሰነድ፣ የአዉሮፓ «ትራስት ፋንድ» እና ሌሎች ፕሮግራሞች በአባል አገራት በተጠናከረ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋል እንዳለባቸዉም ይናገራሉ።


«ሌላኛዉ ቁልፍ ነጥብ ደግሞ አባል አገሮች በአፍሪቃ ቀንድ የጠናዉን የፍልሰት ችግር በተመለከተ ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ መረጃ ማድረስ እንዳለባቸዉ ነዉ። አዎ እኛም ከአፍሪቃ ቀንድ የሚፈልሱ አሉን ይሁን እንጅ በተጠናከረ መንገድ ተመዝግቦ መቀመጥ አለበት። በርከት ያለዉ ፍለሰትም የሚከሰተዉ በአፍሪቃ ቀንድ ነዉ ፣ የአፍሪቃ ቃንድም ከሌሎች የአፍሪቃ ክፍል በበለጠ በግንባር ቀደምትነት ስድተኞችን የሚያስተናግድ አካባቢ ነዉ። ኬንያ እና እትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን ስድተኞች በማስተናገድ ይታወቃሉ። በዚህ አካባቢ ከቦታቸዉ የሚፈናቀሉ ብዙዎች እንዳሉ ሆኖ ቀያቸዉን ጥለዉ የሚሰደዱም በርካታ ናቸዉ።»


እንደ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ፣ በመሳሰሉት የኢጋድ አባል አገራት ያለዉ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚ ሁኔታ ወጣቱን ለፍልሰት እንደሚዳርገዉ ይነገራል። በዚህ ላይ የፍልሰት አሰተዳደር ስብሰዉ ምን መክረዋል?

« በእዉነቱ ስብሰባዉ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አቋም አልያዘም። ግን እኔ የምልህ፣ ሰዎች የሚፈልሱበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። እናም ብዙ ግዜ ፍልሰት እንደ አሉታው ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ ግን አይደልም። ልያሳስበን የሚገባዉ ሰዎች ያለምንም ሕጋዊ ሰነድ ሲንቀሳቀሱ እና ባዛም ሕጋዊ ያልሆነ የሰዉ ዝዉውር ሲደረግ ስናይ ነዉ። ሰዎች ለመሰደድ ብዙ ምክንያት ሊኖራቸዉ ይችላል፣ እነዛም አንዱ ኤኮኖሚ ሊሆን ይችላል፣ ይህ በአፍሪቃ ብቻም አይደልም። አፍሪቃ ከዉጭ ከሰሜን አሜሪካ እና ከአዉሮጳ የፈለሱ ብዙ ሰዎችን ታስተናግዳለች። ሌላዉ ለፍልሰት ምክንንያት የሚሆነዉ የሰዎች ያለፍላጎታቸዉ ከቦታቸዉ መፈናቀል ነዉ። ይህም የፖለቲካ ስርዓት አለመረጋጋት፣ ጭቆና፣ ለምሳሌ በኤርትራ የብሔራዊ ዉትድርና አገልግሎት ግዴታ፤ እንዲሁም ሰዎችም በተፍፈጥሮዊ አደጋ ከመኖሪያቸዉ ሊፈናቀሉ ይችላሉ።»

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ