1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን የበርሊን ማራቶን ድል

እሑድ፣ መስከረም 15 2009

ጀርመን መዲና በርሊን ውስጥ ዛሬ በተከናወነው የማራቶን ሩጫ ፉክክር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት አበሩ ከበደ ድል ተቀዳጁ። አትሌት ቀነኒሳ 42 ኪሎ ሜትሩን የሩጫ ውድድር ያሸነፈው የኬንያው ብርቱ ተፎካካሪ ዊልሰን ኪፕሳንግን ጥሎ በማለፍ ነው።

https://p.dw.com/p/2QZnL
Kenenisa Bekele  Äthiopien Marathon Berlin Deutschland
ምስል picture-alliance/dpa/AP Photo/M.Schreiber

ቀነኒሳ ዛሬ ያሸነፈበት የ2 ሰአት ከ3 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ውጤቱ  በ6 ሰከንዶች ብቻ በመዘግየቱ የውድድሩን ክብርወሰን ለመስበር ሳይሳካለት ቀርቷል። ሆኖም የቀነኒሳ ውጤት የኢትዮጵያ ክብርወሰን መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።  የበርሊን ማራቶን ክብርወሰን የተያዘው ባለፈው ዓመት በዴኒስ ኪሜቶ ነው።  በዛሬው ውድድር ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ ከቀነኒሳ በ10 ሰከንዶች ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ መውጣት ችሏል። ሌላኛው ኬንያዊ ኢቫን ኪፕላጋት ቼቤት ሦስተኛ ሲወጣ፤ ኢትዮጵያዊው ሲሳይ ለማ በአራተኛነት አጠናቋል። በበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድርም ድሉ ከኢትዮጵያውያን እጅ አልወጣም። አበሩ ከበደ በ2:20:45. በማጠናቀቅ አንደኛ መውጣት ችላለች። ኢትዮጵያውያቱ ብርሐኔ ዲባባ እና ሩቲ አጋ ተከትለዋት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል። 

MS/LA