1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ኢትዮጵያ የገቡ  የደቡብ ሱዳን ስደተኞች

ሐሙስ፣ ሰኔ 8 2009

የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔር እንዳሉት ካለፈዉ መስከረም ወዲሕ ብቻ ወደ ዘጠና ሺሕ ያሕል ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል

https://p.dw.com/p/2el2H
Sudanesische Flüchtlinge in Äthopien
ምስል DW/Coletta Wanjoyi

(Beri.AA) Südsudanflüchtlinge in Äthiopien-UNHCR - MP3-Stereo

የደቡብ ሱዳንን ጦርነትና በሐገሪቱ የተከሰተዉን የምግብ እጥረት በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ የሚሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር መጨመሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔር እንዳሉት ካለፈዉ መስከረም ወዲሕ ብቻ ወደ ዘጠና ሺሕ ያሕል ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።አቶ ክሱት አክለዉ እንዳሉት ሥደተኞቹን ለማስተናገድ ድርጅታቸዉ ተጨማሪ መጠለያ ጣቢያዎች ከፍቷልም።ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ