1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በ«ህዳሴ ግድብ» ጥናት አለመስማማቷ ግብፅን አሳሰባት 

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ኅዳር 11 2010

ኢትዮጵያ የምታስገነባዉ የ«ህዳሴ ግድብ» በሱዳንና በግብፅ ላይ ሊያስከትል ይችል ይሆናል የሚባለውን ጉዳት የመረመረው ጥናት የመጀመሪያ ውጤት ላይ ለመወያየት የግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የቴክኒክ ኮሚቴ፣ እንዲሁም፣  የዉሃ ሃብትና መስኖ ልማት ሚንስትሮች ተገናኝተው ነበር።

https://p.dw.com/p/2nx1W
Karte Nil Verlauf und Renaissance-Staudamm Englisch

Egypt, Ethiopia Head-to Head on GERD Study - MP3-Stereo

ይሁን እንጅ ፣ በአንድ ወር ዉስጥ ሁለት ጊዜ የተገናኙት የኮምቴው ተወካዮችና የዉሃ ሃብት ሚንስትሮቹ የግድቡ ግንባታ፣ እንዴት ግድቡ ሳይጀመር በፊት የነበረዉን የዉሃ አጠቃቀም ሁኔታ እና የዉሃዉን አጠቃቀም ይጎዳል በሚለው ጉዳይ ላይ  ሳይስማሙ መቅረታቸዉን የግብፅ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃላቀባይ አህመድ አቡ ዛኢድ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ባሳለፍነዉ ቅዳሜ የግብፁ ፕሬዚደንት አብዴል ፋታህ ኤል ሲሲ ዉድቅ የሆነዉን የጥናት ውጤት በተመለከተ ባደረጉት ንግግር  የዓባይ ወንዝ ለግብፃውያን «ውሃ የህይወት እና ሞት ጉዳይ» ነዉ ሲሉ ኢትዮጵያን አስጠንቅቀዋል። የግብፅ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳሜህ ሹክርም ጉዳዩ ለሀገራቸው እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ለዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቲለርሰን ትናንት ገልጸዋል።

ግብፅ ይህን ጉዳይ በቀላሉ እንደማትመለከተዉ አቡ ዛኢድ አክሎበታል፣ «ይህ ሁኔታ በጣም ወሳኝ ነዉ ብለን ነዉ። ያሉትን የስምምነት ሂደቶች አደጋ ዉስጥ ኢየጣለ ነዉ። በተለይ ኢትዮጵያ ጥናቱ ሳይጠናቀቅ በፊት የግድቡን ዉሃ እንዳትሞላ ቃል መግባቷን የመግባቢያው ስምምነት በግልፅ አስቀምጦታል። የመግባቢያው ስምምነት አንቀጽ አምስት እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ ጥናቱ ከተጠናቀቀ  በኋላ በመጀመሪያው ሙሊት  እና በዓመታዊው የስራ መመሪያ ላይ ከሌሎቹ ሁለት ሃገራት ጋር ስምምነት ትደርሳለች።»

Eco@Africa - Damm
የ«ህዳሴ ግድብ» ግንባታምስል Eco@Africa

የዉሃ ሃብትና የመስኖ ልማት ሚንስትሮቹ እንዲገናኙ ምክንያት የሆነዉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎችና የቴክኒክ ኮሚቴዉ ለወራት ባደረጉት ዉይይት ላይ ስምምነት ላይ ስላልደረሱ ነዉ ሲሉ አቡ ዛኢድ አስታወቀዋል።

ሶስቱም ሃገሮች፣ በተለይም ኢትዮጵያና ግብፅ ስምምነት ላይ ካልደረሱ ወደ ግጭት ልያመራ ይችልል፣ ግጭቱ ደግሞ ለዉሃ ጦርነት በር ይከፍተል ብሎ የሚሰጉ አሉ። በግብፅ በኩል ያለዉ ምልስ አህመድ እንድ ይላሉ፣ «ሶስቱ ሀገራት የተፈራረሙት የመግባቢያው ስምምነት ግብፅ የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት፣ ኢትዮጵያም የዓባይን ውሀ በተመለከተ ያለውን የግብፅን የህልውና ጥያቄ መረዳታቸውን በግልጽ አስቀምጧል። የአባይ ዉሃ ሁሌም የትብብር ምንጭ ፣ የጋራ መግባባት እና ሁሉንም ተፋሰስ አገሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሆኖ ቆይቷል። የሁሉንም ጥቅም ለማሳደግ እና በዚሁ ጉዳይ ሰበብ ሊፈጠር የሚችል ማንኛውንም ዓይነት ጉዳት ለመቀነስ ከተፈለገ ተፋሰስ አገሮች ሁሉ መተባበር አለባቸው ብለን እናስባለን።»

የግድቡን ጥናት እንድያካይዱ ለBRLና አርቴልያ ለተባሉት ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያ ስራዉ የተሰጠዉ ከአስር ወር ገደማ በፊት ነዉ። ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የበለጠ መረጀ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ