ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር
እሑድ፣ ሰኔ 4 2009ማስታወቂያ
ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ መሠረታዊ መብቶች መከበራቸዉን የሚደነግገዉን ሕገ መንግሥት ከማጽደቅ አንስቶ፤ በፖለቲካዊም ሆነ በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ቀላል የማይባሉ ተግባራት መከናወናቸዉን ብዙዎች ይስማሙበታል። ለዉጦቹ ተስፋ ሰጪ ሆነዉ አለመቀጠላቸዉ ግን ወትሮ ይነሱ የነበሩ የሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ የመድበለ ፓርቲ ምሥረታ፤ የሕግ የበላይነት ወዘተ ጥያቄዎች ዛሬም እንዲያስተጋቡ ምክንያት እንደሆኑም በሰፊዉ ይታመናል። ኢትዮጵያ አሁን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ትገናለች። ሌላስ? ለ26 ዓመታት በኢህአዴግ የምትተዳደረዉ ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ አድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ