1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ፤ የጀርመን ባለስልጣን «የአፍሪቃ ማርሻል እቅድ»

ማክሰኞ፣ መጋቢት 26 2009

አዲስ አበባ ዉስጥ መግለጫና ማብራሪያ የሰጡት የጀርመኑ የልማት ተራድኦ ሚንስትር እንዳሉት ለአፍሪቃ የሚደረገዉ ርዳታም በማርሻል ዕቅድ ዓይነት ካልተመራ አህጉሪቱ ከችግር አረንቋ አትወጣም።

https://p.dw.com/p/2agOg
Äthiopien Bundesentwicklungsminister Gerd Müller in der Somali-Region
ምስል picture-alliance/dpa/K. Nietfeld

(Beri.AA) Müllers besuch in AA - MP3-Stereo

የጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስትር ጌርድ ሙይለር «የአፍሪቃ ማርሻል እቅድ» ያሉትን ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪቃ ላይ ይፋ አደረጉ። የጀርመን የዜና ወኪል ዲፒኤ እንደዘገበዉ፤ ሙይለር ዛሬ አዲስ በአበባ ከአፍሪቃ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የሥልጠና ዘመቻ ለማካሄድ እና የአፍሪቃን ጥሬ ሃብት ያለ አግባብ መጠቀምን ለማስቆም ቃል ገብተዋል። የማርሻል ዕቅድ የሚባለዉ፤ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦነርት በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ አዉሮጳን መልሶ ለመገንባት ያቀደችዉ መርሃግብር በመሆኑ በታሪክ ይታወቃል። እንደዘገባዉ በጀርመን መንግሥት ከአፍሪቃ ጋር የታሰበዉ የማርሻል ዕቅድ ማሻሻያዎችን መሠረት ያደረገ ነዉ።  ሙስናን የሚዋጋ፤ የግብር ሥርዓትን መገንባት የሚሻ፤ ትምህርት ላይ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈስ እና በፆታ እኩልነት ላይ መሠረት ያደረገ ከዚህ ከጀርመን መንግሥት ዕቅድ ተጠቃሚ እንደሚሆን ነዉ የተገለጸዉ። የጀርመኑ አረንጓዴ ፓርቲ ግን የሚኒስትሩ ዕቅድ ተጨባጭ ነገር የለዉም በሚል ይከሳል። ሆኖም ከአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን  ምክልት ፕሬዝደንት ክዋሲ ኩዋርቴ ጋር ባደረጉት ንግግር ሙይለር «ማንም እንዴት እንደሚደረግ እኔ አዉቃለሁ የሚል እንደሌለ» የእሳቸዉ ዕቅድም በአዉሮጳ ኅብረትና በአፍሪቃ ሃገራት መካከል በሚካሄድ ድርድር እንደሚወሰን አመልክተዋል። አክለዉም፤

« የልማት እድገት ለሰላም የሚያስፈልግ እና ጦርነትንም የሚከላከል ነዉ። እናም በአፍሪቃ አህጉር የግል የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ለማስፋፋት፤ በግል መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ አዲስ ትኩረት አድርገናል፤ መልካም አስተዳደርን በማጠናከር ማስፋፋት እንዲሁም በመጠየቅ። በአዉሮጳ እና በአፍሪቃ መካከል ያለዉ የንግድ ግንኙነት ፍትሃዊ አይደለም፤ ፍትሃዊ የንግድ ግንኙነት ያስፈልገናል።»

ከዚህም ሌላ ሙለር ወታደራዊ ኃይል በመገንባት ሰላምን ማምጣት እንደማይቻልም አመልክተዋል። በሚኒሥትሩ የቀረበዉ የተነሳሽነት ሃሳብ ወደአዉሮጳ የሚደረገዉን ሕገወጥ ስደትም ለመቀነስ ያለመ እንደሆነ ነዉ የተገለጸዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚንስትር ጌርድ ሙለር አፍሪቃን ከሰብአዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት ለማዉጣት፤ አሜሪካኖች በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማብቂያ ለአዉሮጳ የነደፉት ዓይነት ዕቅድ ያስፍልጋታል አሉ። በያኔዉ የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስር በጆርጅ ማርሻል ሥም የተሰየመዉ ማርሻል ፕላን በጦርነት የወደመችዉ አዉሮጳ ዳግም እንድታንሰንሰራራ በጅጉ ጠቅሟል። ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ መግለጫና ማብራሪያ የሰጡት የጀርመኑ የልማት ተራድኦ ሚንስትር እንዳሉት ለአፍሪቃ የሚደረገዉ ርዳታም በማርሻል ዕቅድ ዓይነት ካልተመራ አሐጉሪቱ ችግር አረንቋ አትወጣም። ዝርዝሩን ከጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ እንስማ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ