1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ አበባ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት መግለጫ እየተጠበቀ ነው

ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2010

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (የኢሕአዴግ) ምክር ቤት ዛሬ ማምሻዉን የፓርቲዉን አዲስ ሊቀመንበር ማንነት በይፋ ያስታዉቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ። ከአዲስ አበባ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ምክር ቤቱ በሁለት ሳምንት ስብሰባዉ ሥለደረሰበት ዉሳኔ  ለሐገር ዉስጥ ጋዘጠኞች መግለጫ ለመስጠት ጋዜጣዊ ጉባኤ ጠርቷል።

https://p.dw.com/p/2v5gp
EPRDF Logo

 ወኪሎቻችን  እንደገለፁልን በጋዜጣዊዉ መግለጫዉ ላይ ለዉጪ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘግቡ ጋዜጠኞች አልተጋበዙም። የኢሕአዴግ  ሊቀመንበርነት እና የሐገሪቱ ጠቅላይሚንስትር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸዉን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ የግንባሩ ምክር ቤት ዛሬ ማፅደቁን የተለያዩ የሐገር ዉስጥ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል። በኢትዮጵያ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ድረስ በመገናኛ ብዙሃን የቀረበ ምንም መግለጫ የለም።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ