ጡረተኞቹ ስደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል” በሚል ተፈርዶባቸዋል
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2010ማስታወቂያ
የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በጡረተኞቹ ላይ ብይን ያስተላለፈው ባለፈው ዓመት በፈረንሳይ እና ጣሊያን ድንበር አካባቢ ሕጻናትን ጨምሮ ስድስት ስደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል፣ ሕግም ተላልፋችኋል” በሚል ነበር፡፡ የተከሳሾቹ የይግባኝ ውሳኔ ከተሰማ በኋላም ፈረንሳይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍም ወጥተዋል፡፡ ይህ መሰሉ ንቅናቄ በፈረንሳይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየታየ ባለው የስደተኞች አቀባበል ችግር ላይ መሻሻል እንዲኖር ግፊት እንደሚፈጥር እየተነገረ ነው፡፡ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከሳሾቹን ጡረተኞች አነጋግራ ያጠናቀረችውን ሙሉ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ