አነጋጋሪው የግሪክ አዲስ ሃሳብ
ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2007ማስታወቂያ
የግሪክና የአበዳሪዎቿ ውዝግብ መፍትሄ ሳያገኝ ግሪክም ከአበዳሪዎቿ ትጠብቅ የነበረውን ገንዘብ ሳታገኝ ዕዳዋንም ሳትከፍል የተሰጣት የጊዜ ገደብ አልፏል ። የጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ትናንት የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲሲ ሲፕራስ ለአበዳሪዎች ባቀረቡት አዲስ ሃሳብ ላይ አበዳሪዎች ዛሬ ይነጋገሩበታል ። የግሪክ መንግስት አልቀበልም ባለው አበዳሪዎች ባስቀመጧቸው ቅድመ ግዴታዎች ላይ የግሪክ ህዝብ ድምፅ እንዲሰጥ ጠይቆ ለአበዳሪዎች አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡ እያነጋገረ ነው ። መፍትሄ ስላላገኘው የግሪክና የአበዳሪዎች ውዝግብ የብራሰልሱ ዘጋቢያችንን ገበያው ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ