1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መረጃ መቆጣጠሪያ ስልት

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ሐምሌ 18 2008

Freedom House ባወጣዉ ዘገባ ከዓለማችን 7,4 ቢሊዮን ህዝብ 13 በመቶ ብቻ ነፃ ፕሬስን እንደሚጠቀሙ ያመለክታል። ቀሪዉ 41 በመቶ በግማሽ ነፃ ሲሆኑ፣ 46 በመቶ ደግሞ ምንም ዓይነት ነፃ የመገናኛ ብዙሃንን በሉለበት እንደሚኖር ዘገባዉ ጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/1JVgS
Karte Äthiopien englisch

[No title]

ኢትዮጵያ አዲስ እና ዉስብስብ የሆነ ሳንሱር የማድረግያ እና መረጃ መቆጣጠርያ ዘዴ በመጠቀም፣ እንዲሁም በሽብር ላይ የምታደርገዉን ጦርነት ሰበብ በማድረግ ጠንካራ የሆኑ ሕጎችን ተጠቅማ ዜጎቿን እንደምትቀጣ፣ በዚህም ምክንያት «NOT FREE» ወይም የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የሌለባት አገር ሲል ጠቅሷል።
በአገርቱ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ተጠቅመዉ ሃሳባቸዉን የሚገልፁ እንዲሁም መንግሥትን ከሚተቹት ዉስጥ የድረገጽ ጸሐፊዉ በፍቃዱ ኃይሉ አዲስ እና ዉስብስብ ቴክኖሎጅ መንግሥት ይጠቀማል ስለመባሉ እንደሚከተለዉ ይጠቅሳል፣
ከድረ ገጽ ጸሐፊነቱ ጋር በተያያዘ ክስ ወደ ሁለት ዓመት ገደማ እስር ላይ ቆይቶ የወጣዉ በፍቃዱ ብዙ ግዜ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ መንንግሥት የፖለትካ ተቃዋሚዎችን እና ጋዜጠኞችን የሚከሰዉ የስልክ ምልልሶቻቸዉን በመጥለፍ ነዉ ይላል። ይህንንም ጠለፋም ወይም «malware software» ተጠቅሞ የኮምፕዩተር መረጃ ብርበራ ሲያካሄድ በሕጋዊ መንገድ ከፍርድ ቤት በተፈቀደ ትዛዝ እንዳልሆነም ይነጋራል። እንደ ማስረጃነት እሱ እና ሌሎች የድረገጽ ጸሐፍት ላይ ሲቀርብ የነበረዉን እንዲህ ያስረዳል።መንግስት አብዛኛዉ ግዜ ይህን ርምጃ ሲወስድ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል እንደሆነ እና ርምጃ የሚወስድባቸዉ ተቃዋሚ ፖለተከኞችም ሆኑ ጋዜጤኞች ሌላ ተልዕኮ አላቸዉ ሲል ይከሳል። አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ በረከት ስዩም ደግሞ እንዲህ ይላሉ፣
መንግሥት ባለፉት ቀናት ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ማለትም ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ዋትስኣፕ እንድሁም ቫይበርን ዘግቶ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ቀስ በቅስ ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቀናት መክፈት መጀመሩን ተጠቃሚዎች ይናገራሉ። የተዘጋዉ ተከፈተ ይባል እንጂ አጥጋቢ እንዳልሆነ እንዲሁም መንግሥት በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ እንዲህ አይነቱ ርምጃ መዉሰዱ በአገሪቱ ምን ያህል ሃሳብን በነፃነት መግለፅን እንዳፈነ በፍቃዱ ይዘረዝራል።
በዶቼ ቬለ የፌስ ቤክ ገፃችን ላይ አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ «ታፍነናል»መንግሥት የሚወስዳቸዉ ርምጃዎችንም «አስነዋሪ ተግባር» ሲሉ የተቹ አሉ። አንዳንዶች ደግሞ መንግሥት ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ አኳያ የሚወስዳቸዉን ርምጃዎች ባይደግፉም በቅርቡ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንን መዝጋቱ ተገቢ ነዉ የሚል አስተያየታቸዉን ይሰጣሉ።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ