ውይይት፦አቤቱታ ያስከተለዉ የግምት ገቢ ግብር ትመና
እሑድ፣ ሐምሌ 9 2009ማስታወቂያ
ብዙዎቹ የቀን ገቢ የግምት ስሌቱ እና ዓመታዊ ሽያጫቸዉ ይሆናል በሚል ተጣለብን ያሉት የግብር መጠን የተጋነነ እና ከአቅማቸዉ በላይ እንደሆነ ይናገራሉ። አቤቱታቸዉንም ከመገናኛ ብዙሃን አልፈዉ ለሚመለከተዉ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽሕፈት ቤት ለማቅረብ እንደሞከሩ ይገልጻሉ። ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ የነጋዴዎቹን የቀን ገቢ የገመተበት ጥናት ማድረጉን ይናገራል። ባካሄደዉ ቅኝት መሠረት የደረጃ ለዉጦች ያንንም ተከትሎ የግብር ለዉጥ መኖሩንም ያስረዳል። በዚህም መሀል ግብር ከፋዮች ከገቢያችን በላይ ግብር ተጠየቅን በማለት እያማረሩነዉ። ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ የቅሬታዉን መንስኤ እና መፍትሄን ለመቃኘት ያካሄደዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ