አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቱሪዝም ላይ ተጽዕኖ አላደረሰም ተባለ
ሰኞ፣ መጋቢት 3 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚል ሥጋት በተደጋጋሚ ቢደመጥም ወደ አገሪቱ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎች ቁጥር አለመቀነሱን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ይኸን ያሉት በየዓመቱ በጀርመኗ በርሊን ከተማ በሚካሔደው የቱሪዝም ኤክስፖ የታደሙት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ይቻል ምሕረት ናቸው።
እንደ አቶ ይቻል አባባል ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎች ቁጥር ካለፈው አመት ጋር ሲነፃጸር በ10 በመቶ እድገት አሳይቷል። አሜሪካ እና ብሪታኒያን ጨምሮ በርካታ አገራት ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ሲመክሩ ከርመዋል። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ምን ተፅዕኖ አሳድሯል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ