በአቶ ኃይለ ማርያም ሥልጣን መልቀቅ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች
ዓርብ፣ የካቲት 9 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣን እለቃለሁ ማለታቸው በጎ ነው ሲሉ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ። ሆኖም ለዶቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን የህዝብ ጥያቄ የግለሰብ ለውጥ ሳይሆን የስርዓት ለውጥ መሆኑን ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ዶቼቬለ አስተያተቱን የጠየቀው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጉዳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ መሆኑን አስታውቆ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቅ ለወደፊቱ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ተስፋን የሚያበረታታ ነው ማለቱን ከዋሽንግተን መክበብ ሸዋ ዘግቧል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ