1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሮጌ ቧንቧን በአዲስ የሚተካ ቴኬኖሎጅ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2008

ኤላስቶቴክ ይባላል። ሥራዉም ባሮጌዉ ወይም ተሰንጥቆ ፈሳሾችን በሚለቅ ቧምቧ ዉስጥ ግርግዳዎችን ሳያደራምሱ ወይም ወለሎችን ሳያፈርሱ አዲስ ቧንቧ መግጠም ነዉ።

https://p.dw.com/p/1HZOd
Stahlröhre auf Halde
ምስል AP

[No title]

የኤላስቶቴክ መሰሪያን የሚያመረተዉ Relining Group ተብሎ የሚጠረዉ የፊንላንድ ኩባንያ ነዉ። ኩባኒያዉ መሳርያዉን ማምረት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የቆሻሻ ወይም የፈሳሽ ቧንቧዎችን ዲዛይን የማድረግ፤ የማምራት እና የማከፋል ስራ ይሰራል። 80 ኪሎግራም የሚመዝነዉ ይህ ኤላስቶቴክ መሳርያ 1080 ሚሊሜትር ቁመት እና 570 ሚሊሜትር ስፋት ያለዉ ሲሆን በአድሱ ቴክኖሎጂ ማለትም ቧንቧዉ ዉስጥ በተገጠመለት ካሜራ፣ በtouch screen የሚዳሰስ እና በርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ የሚቆጣጠር ገፂታዎች እንዳሉት ይናጋራል። እንደ Relining Group ደህረ ገፅ መረጃ ከሆነ ኤላስቶፍሌክ ተብሎ የሚጠራዉ መሳሪያ በአሮጌዉ ቧንቧ ዉስጥ ሳይተክል በፊት አሮጌዉን ቧንቧ ያፀዳዋል፣ ከዛም ካደረቀ በዋላ አዲሱን ኤላስቶፍሌክን ይተክላል።አዲሱ ቧንቧ ሲተከል አሮጌዉ ቧንቧ ሳይጎዳ እንደሆነ ኩባንያዉ ያስረዳል።
ቴክኖሎጂ በአሜርካና በአዉሮፓ ወደ 25 ዓመታት ቢያስቆጥርም እያደጉ አገራት ዉስጥ ብዙም ታይቶ እንደማይታወቅ ለመሳርያዉ ቀሬቤታ ያላቸዉ አንዳንድ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

ቴክኖሎጂ በአሜርካና በአዉሮፓ ወደ 25 ዓመታት ቢያስቆጥርም እያደጉ አገራት ዉስጥ ብዙም ታይቶ እንደማይታወቅ ለመሳርያዉ ቀሬቤታ ያላቸዉ አንዳንድ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ቴክኖሎጂዉ ለአፍርቃም ሆነ ለኢትዮጵያ አዲስ መሆኑን የሚናገሩት የTSS Pipe አምራች ስራ አስካያጅ አቶ መብት አብራሃም ተክኖሎጂዉን ለመጀመርያ ግዜ ያመጡት እሳ,ቸዉ መሆን እና እንዴት እንዳመጡት ሲናገሩ፣ በፍንላንድ ስኖሩ በአጋጣም ከመሳርያዉ አምራች ባለቤቶች ጋር ተገናኝቶ እንደነበር እና ቴክኖሎጂዉ ለእትዮጲያ አስፈላግ መሆኑን ካዩት በዋላ ነዉ። በእትዮጲያ ለማስተዋወቅ ለባለቤቶቹ አሰቡን ካቀረቡት በዋላ በእነሱ የገንዘብ እገዛ ወደ አገርቱ ማምጣት ችለዋል።


እንደ Relinig Group ከሆነ ይህን መሳርያ እንዲ ገነባ ያስገደደዉ ደነበኞቹ ብዙ ፍላጎት ስላሳዩ ሲሆን፣ ደንበኞቹም ብዙ ወጭ ሳያወጡ የተበላሸዉን ቧንቧ ማደስ እንዲችሉ አድርጎታል ይላል። በኢትዮጵያም ብዙ ደንበኞች እንዳሉት አቶ መብት አብራሐም ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ለመኖሪያ ቤት፤ ለሆቴሎች፣ለትምህርት ቤቶች፣ ለፋብርካዎች እና ለሆስፒታሎች፣ የሚያገለግለዉ ይህ መሰርያ አሮጌ ቧንቧዎችን ሳይነሱ፣ ግርግዳዎች ወይም ወለሎች ሳያፈርሱ አዲሱን ቧንቧ መግጠም መቻሉ ነዉ ለየት የሚያደርገዉ። አቶ መብት አብራሃም ይህ ቴክኖሎጂ ከነዳጅ ቧንቧዎች ጀምሮ እስከ መወኛ ገንዳ ቧንቧዎች ዉስጥ ከ40 ሚሊሜትር እስከ 200 ሜትር ድያሜትር ያለዉ ቱቦ መገንባት እንደሚችልም ተናግሮዋል።

Stahl in China - Rohre Stahlröhre
ምስል picture-alliance/dpa


እንደ ጎርጎሮሳዉያኖቹ አቆጣጠር በ2013 የኤላስቶፍሌክ ማቴሪያሎች ጥራቱን ለማረጋገጥ በጣም ዉስብስብ የሆነ የ VTT የበለሙያ አገልግሎት ተብሎ የሚጠረዉ ቅደመ ሁነታዎች እንዳለፈ የ Relinig Group ድረ ገፅ ያትታል። የVTT Expert Sevices Ltd ወይም የባለሙያ አገልግሎት የሚሰጠዉ የጥራት ወረቀት መሳርያዉ የሚሰጠዉ አገልግሎት ሃሳብ ዉስጥ በማስገባት የሙከራ፣ በጥንቃቄ መመርመር እናም የቧንቧዉን ስፋት እና ፈሳሽ የመሸከም አቅሙን ይለካል። ይህ አድሱ ቴክኖሎጅ የሚሰራዉ ምን ያህል ዋስትና እንዳለዉ አቶ መብት ስጠየቁ መልሳቸዉ የነበረዉ በስውድን ያለዉ ጥራት የምያረጋግጥ ኩባኒያ ለ25 ዓመት ምንም አይነት ችግር ሳያጋጥመዉ ቱቦዉ እንደምሰራ ስርትፍኬት እንዳገኙ ነዉ።


ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጲያ የዉጭ ኩባንያዎችም ሆኑ በአገር ዉስጥ ያሉት በመኖርያ ቤቶች እና በፋቢርካዎች ግንባታ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እየጨመረ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ። እንዲሕ ያለ ቴክኖሎጂ ወደ አገርቱ መምጣቱ የቧንቧ ችግሮች ሲፈጠሩ ችግሩ የተፈጠረበትን ቦታ ከማፍረስ ይልቅ አሮጌዉ ባለበት አድስ መትካል መቻሉ ለገንቢዎችም ሆነ ለቤቶቹ ወይም ለፈብርካዎቹ ባሌቤቶች ትልቅ እፎይታ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ያብራራሉ። ይሁን እንጅ ይህን ቴኬኖሎጂ ወደ ኢትዮጲያ ከማስገባታቸዉ በፊት ገበያዉን ያጠኑት ጥናት እንደነበር እናም ከምመለከተዉ አከል ጋር ተዋያይቶበት እንደሆነ ይናገራሉ። ወደ ስራa ባይገቡም ገና ገባያዉ ዉስጥ ቴክኖሎጂዉን እያስተዋወቁ መሆናቸዉን ይናገራሉ።


አቶ መብት ባደረጉት ጥናት በዓመት ከ15-20 የሚደርሱ ደንበኞች ሊኖራቸዉ እንድሚችል ተናግሮዋል። ይህን መሳርያ ከገባያዉ ጋር ለማስተዋወቅ ብዙ ወጭ እንደወሰደባቸዉ እና መሳርያዉ ብቻ እስከ 60,000 ዩሮ እንዳወጡበት ይናገራሉ።
የእላስቶፍሌክ ቱቦ በኮንክርትም ሆነ በብረት፣ በፒላስትኪም ሆነ በኮፕፔር ወይም አይሬን የተሰሩት አሮጌ ቧንቧዎች ዉስ ሊገጠም እንደምችል ኩባኒያዉ ያስረዳል። ከዛም አልፎ ፀረ ባክቴርያ መሆኑን እና የሚለዋወጠዉን የአየር ፀባይ መቋቋም እና ለረጅም ግዜ ሳይዝግ ወይም ሳይበላሽ መቆየት እንደምችልም በድረ ገፃቸዉ አስቀምጦታል።


መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ