1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
12 ምስሎች
ረቡዕ፣ ሰኔ 7 2009
https://p.dw.com/p/2eh9n

በኢትዮጵያ የጀርመን እና የአፍሪቃ ኅብረት አምባሳደር በመሆን ያገለገሉት ዮአኺም ሽሚት ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማዉ በድንገት ነዉ። በአፍሪቃ ኅብረትም የጀርመን አምባሳደር የነበሩት ዮአኺም ሽሚት ወደ ኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ተሾመዉ የሄዱት በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር ከሐምሌ 2014 ጀምሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸዉ አስቀድመዉም በቦስኒያ ሄርዞጎቭኒያ እና ሰርቢያም በአምባሳደርነት አገልግለዋል። አምባሳደር ዩአኺም ሽሚት በኢትዮጵያ እጅግ ተወዳጅ እና ታዋቂ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር እጅግ ቅርበት አላቸዉ ከሚባሉ የዉጭ ሃገራት አምባሳደሮች ቀዳሚዉን ስፋራ የሚይዙ ነበሩ።