1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኔዘርላንድስ የኤርትራን ዲፕሎማት ማባረሯ

ዓርብ፣ ጥር 11 2010

የኔዘርላድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሀገሩ የሚገኙትን አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ዲፕሎማት እንዲባረሩ መወሰኑን ትናንት በዓለም ዜና መዘገባችን ይታወሳል። ውሳኔው በውጭ ከሚገኙ የሀገሩ ተወላጆች የኤርትራ መንግሥት ዉጭ ሀገር የሚኖሩ ወይም ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ላይ ከሚሰበስበው ግብር ጋር የተያያዘ መሆኑም ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/2rAUF
Eine afrikanische Insel der Architektur
ምስል DW/Y.Tegenewerk

«ምክንያቱ ውጭ ከሚኖሩ ዜጎች ግብር መሰብሰብ ነዉ»

 የሆላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀልቤ ዜሌስትራ፤ ባወጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ዉሳኔው የተላለፈው በሀገራቸው የሚኖሩ ኤርትራውያን ለኤርትራ መንግሥት ግብር እንዲከፍሉ የማስገደድ እና የማስፈራራት ተግባር የሚፈጸምባቸው በመሆኑ እና፤ ይህ እንዳይደረግም ኔዘርላንድስ በተደጋጋሚ ያቀረበችው ጥያቄ ተግባራዊ ባለመሆኑ እንደወነ አመልክተዋል። ከብራስልስ ገበያው ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ