ኢትዮጵያዊዉ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 15 2010ማስታወቂያ
የመዝገብ ስሙ ኃይለሚካኤል ጌትነት ይባላል። ብዙዎች የሚያውቁት ኃይሌ ሩትስ በተሰኘ የመድረክ ስሙ ነው። የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ነው። «ችጌ »በሚል መጠሪያም የሬጌና የችክችካ ስልትን በአንድ ላይ ያጣመረ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ ጆሮ አብቅቷል። በረጅም ፀጉሩ እና ለየት ባለ አለባበሱ ቶሎ ከአይን ይገባል። በቅርቡ በስፔን አገር በተካሔደው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ላይ ተጋብዞ ሙዚቃዎቹን አቅርቧል። ከመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ኃይሌ ሩትስ ጋር የነበረንን ቆይታ የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ፀሀይ ጫኔ
ሸዋዬ ለገሠ