1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብ

ኃይሉ መርጊያ በኮሎኝ

Eshete Bekeleእሑድ፣ ጥር 14 2009

ወርቃማው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ጊዜ ተብሎ በሚታወቀው 19 60ዎቹ ስራዎቹን በማቅረብ ገናና የነበረው ኃይሉ መርጊያ ለበርካታ ዓመታት ከመድረክ ርቆ ነበር፡፡ የዛሬ አራት ዓመት ግድም የመሳርያ ቅንብሮቹ በዲጂታል ተቀርጸው ዳግም ለገበያ ከበቁ በኋላ ዝናው በዓለም ይናኝ ይዟል፡፡ በሚኖርበት ዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ ግዛቶችም ሆነ በአውሮፓ ሀገራት እየተዘዋወረ አኮርዲዮኑን እና ፒያኖውን ማናገር ከጀመረ ሰነበተ፡፡

https://p.dw.com/p/2WDoW

በዚህ ዓመት መባቻ ላይም በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ዝግጅቶቹን አቅርቧል፡፡ ከእነዚህ ከተሞች ውስጥ አንዷ የነበረችው የጀርመኗ ኮሎኝ ከተማ በጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም የኃይሉን አስደማሚ ሙዚቃዎች የማድመጥ ዕድል አግኝታለች፡፡ ኃይሉ በትውልድ ኢትዮጵያ ከሆነችው ሲዊዲናዊት ዘፋኝ እና የሙዚቃ አቀናባሪ ሶፍያ ጄርንበርግ ጋር በመሆን የተለያዩ ኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን አቅርቧል፡፡ የኃይሉን የሙዚቃ ዝግጅት የታደመው እሸቴ በቀለ ያጠናቀረውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ መስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ