1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ ምላሽ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 9 2009

አስተያየት ሰጭዎቹ የታራምፕ ምላሽ የዘገየ ነው ብለዋል። የዋሽንግተን መንግሥትም ችግር የሌለ ማስመሰሉንም ተችተዋል።

https://p.dw.com/p/2iHbY
USA PK von Donald Trump zur rechten Gewalt in Charlottesville
ምስል Getty Images/C. Kleponis

ትራምፕ የነጭ የበላይነት አቀንቃኞችን አወገዙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቨርጂንያ ግዛት ብጥብጥ ያስነሱ እና ጥቃት ያደረሱ የነጭ የበላይነት አራማጆችን ትናንት በስም ጠርተው አውግዘዋል። ትራምፕ ከዚያ በፊት እነዚህ ወገኖች በስም ጠርተው ባለማውገዛቸው በተደጋጋሚ ሲወቀሱ ነበር። አስተያየት ሰጭዎቹ የታራምፕ ምላሽ የዘገየ ነው ብለዋል። የዋሽንግተን መንግሥትም ችግር የሌለ ማስመሰሉንም ተችተዋል። ችግሩ ትኩረት ካልተሰጠው ሌላ አደጋ ማስከተሉ እንደማይቀር ለዶቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ ተንታኝ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ