1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክ ከ«አይሲስ» ጋር የሚታደርገዉ ትግል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 14 2008

ምዕራባውያን ሀገራት ራሱን «እስላማዊ መንግስት» ብሎ በሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምሩ ቱርክ ጥምረቱን ለመቀላቀል ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶባታል።

https://p.dw.com/p/1HC0b
Türkei Grenze Syrien Kobane Soldaten Kämpfe Rauch
ምስል Getty Images/AFP

[No title]


በኢራቅና ሶርያ «እስላማዊ መንግስት» መስርቻለሁ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ታጣቂዎችንም ይሁን የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ቱርክ እንድትቆጣጠር ለማድረግ ብዙ ውትወታን ፈልጋ ነበር። በስተመጨረሻ ቱርክ በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች። በሌላ በኩል በቱርክ የተለያዩ ከተሞች ሰሞኑን በ «አይሲስ» አሸባሪዎችና ደጋፊችን በማደን በተካሄደዉ አሰሳ ከሶስት ሽህ የሚበልጡ ታጣቂዎች ወደ ቱርክ ሀገር ዘልቀዉ እንዳይገቡ ባለፈዉ ዓመት የቱርክ መንግሥት እንዳደረገ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። በዚህ በያዝነዉ የጎርጎርዮስ ዓመት ብቻ ከ 1000 የሚበልጡ ራሳቸዉን « እስላማዊ መንግሥት ነን ብለዉ የሚጠሩ አባላት ከነትጥቅ መሳርያና ቦንባቸዉ ድንበር ሊሻገሩ ሲሉ እንደተያዙ ተመልክቶአል።


ዩልያ ሃን / ይልማ ኃይለሚካኤል


እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ