ቦልተን፤ አዲሱ የትራምፕ የፀጥታ አማካሪ
ዓርብ፣ መጋቢት 14 2010ማስታወቂያ
ትራምብ በዙሪያቸዉ የሚገኙ ባለስልጣኖችን የሚለዋዉጡበት ርምጃቸዉ ሳልጣን ላይ ከወጡ ለ14ኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ተንታኞች የትራምፕ ሹም ሽር በአስተሳሰባቸዉ የሚስማሙ እና የዉጭ ፖሊሲያቸዉን እሳቸዉ የሚፈልጉትን ኃይል የቀላቀለ አካሄድ የሚፈግፉ ሰዎችን የማሰባሰቢያ ስልት እንደሆነ ይናገራሉ። ከ10 ዓመታት በፊት በተመድ የአሜሪካን አምባሳደር ሆነዉ ያገለገሉት ዲፕሎማት እና የሕግ ባለሙያ የፊታችን ሚያዝያ 1 ቀን 2010ዓ,ም አዲሱን ሥራቸዉን በይፋ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። አምባሳደር ጆን ቦልተን ማን ናቸዉ? ወደዋሽንግተን በመደወል ዘጋቢያች ከናትናኤል ወልዴ ጋር በአጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ናትናኤል ወልዴ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ