1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ምርመራ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 26 2009

የእስራኤል ፖሊስ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላር በሥጦታ ተቀብለዋል የሚል ክሥ የቀረበባቸውን ጠቅላይ ሚኒሥትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ሶስት ሰዓታት የፈጀ የምርመራ ቃለ-መጠይቅ አድርጎላቸዋል

https://p.dw.com/p/2VCb9
Israel Benjamin  Netanyahu
ምስል picture alliance/dpa/A.Sultan

Q&A Police question Netanyahu as part of corruption probe - MP3-Stereo

ኔታንያሁ በእየሩሳሌም ከሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ ከመመርመራቸው በፊት ግን ምን ጥፋት አልፈጸምኩም ሲሉ ውንጀላውን አስተባብለዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን የሙስናው ቅሌት ጠቅላይ ምኒሥትሩን ከሥልጣን ሊያወርድ ገዢውን ፓርቲም ሊጎዳ ይችላል እያሉ ነው። በእስራኤል የሚገኘው ዜናነሕ መኮንን እንዲህ አይነት ክሶች በእስራኤል የተለመዱ ናቸው ሲል ገልጾልኛል። ለመሆኑ የጠቅላይ ሚኒሥትሩ ክስ የት ያደርሳቸው ይሆን? ዜናነሕ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥቶኛል።


ዜናነሕ መኮንን
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ