የአዲስ አበባ መስተዳድር ርምጃ ዉጤት
ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2008ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ መስተዳድር «በሕግ ወጥ መንገድ የተሠሩ» በሚል ሰበብ መኖሪያ ቤታቸዉን ያፈረሰባቸዉ የከተማይቱ ነዋሪዎች በመጠለያ እጦት እየተሰየቃዩ መሆኑን አስታወቁ። ነፋስ ስልክ-ላፍቶ በተባለዉ አካባቢ የነበረ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ቤታቸዉ በመፍረሱ ምክንያት ልጆቻቸዉን በየሥፍራዉ ለመበተን፤ በሽተኛ የቤተ-ሰብ አባል ሳይቀር ሜዳ ላይ ለመዉደቅ ተገድደዋል።ባሁኑ ወቅት እየጠነከረ የመጣዉ የክረምት ዝንብና ቁርም እያሰቃያቸዉ ነዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ችግረኞቹን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ