1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ባሕል መንገድን ይመራል» ፕሮጀክት በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ግንቦት 23 2010

መቀመጫዉን በስዊድንና በኢትዮጵያ ያደረገዉ ሰላም ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ድርጅት ባህል ላይ ያተኮረ የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ቀርፆ ሥራዉን ጀምሯል።

https://p.dw.com/p/2yhxX
Selam Äthiopien Logo
ምስል Selam Ethiopia

ሰላም ኢትዮጵያ የባህል ድርጅ

«Culture Lead the Way ወይም ባሕል መንገድን ይመራል» የሚል ርዕስ ያለዉ ይህ ፕሮጄክት በሙዚቃ፤ በፊልም፤ በመገናኛ ብዙሃንና በሰርከስ ትርኢት በአዲስ አበባ፤ በኦሮሚያ፤ አማራ፣ ትግራይ እና በደቡብ ብሔር፤ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተግባራዊ ለማደርግ ማቀዱን የድርጅቱ መሥራችና ዋና ኃላፊ አቶ ተሾመ ወንድሙ ይናገራሉ። ይህን ለማከናወንም በተጠቀሱት አምስት ቦታዎች ዉስጥ ካሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፤ የባህል ቢሮዎችና አንዳንድ የሙዚቃ ማህበሮች ጋር በመተባበር እንደሚሰሩም አቶ ተሾመ ያክላሉ።

ሰላም ኢትዮጵያ የባህል ድርጅት አገሪር ዉስጥ መስራት ከጀመረ ከ10 ዓመት በላይ ማስቆጠሩን የሚናገሩት የድርጅቱ መሥራችና ዋና ኃላፊ አቶ ተሾመ በአዲስ አበባ ባላቸዉ የሙዚቃ ስቱዲዮ የተለያዩ የባሕል ሥራዎችን እንደሰሩ አክለው ገልጸዋል።

Selam Äthiopien Teshome Wondimu
አቶ ተሾመ ወንድሙ፣ የሰላም ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ኃላፊምስል Selam Ethiopia

ለሶስት ዓመት የሚዘልቀዉ አዲሱ ፕሮጄክት ባለፈዉ ወር አጋማሽ መጀመሩን የሚገልጸው ሰናይ መኮንን የአማርኛ የሂፖፕ ሙዚቃ ዘርፍ ላይ መሰማራቱን ይናገራል።

በአገሪቱ የሙዚቃ ወይም የፊልም ኢንዱስትሪ አለ ማለት አንችልም የሚሉት የሰላም ኢትዮጵያ የድርጅት መሥራችና ዋና ኃላፊ አቶ ተሾመ ወንድሙ ከጅምሩ መዋቅርና ስረዓት አለመገንባቱን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። የትምህርት እጥረት፤ የሙያዉ ማህበሮች አለመደራጀትና መንግሥት የያዘዉ የተለያዩ ፖሊሲዎች ለኢንዱስትሪዉ መዳከም አስተዋሕፆ እንዳላቸዉም አክሎበታል።

የሶስት ዓመቱ ፕሮጀክት የተጀመረው ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ ጋር በመተባበር መሆኑን ከድርጅቱ ድረገፅ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል። በዋናነትም«Culture Leads the Way» የተሰኘዉን ፕሮጄክት በገንዘብ የሚደግፈዉ የስዊዲን የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ በምፃሩ SIDA መሆኑም ተጠቅሰዋል።

Selam Äthiopien Torbjörn Pettersson
ቱርብያን ፐተርሾን፤ የስዊድን ኤምባሲ አምባሳደርምስል Selam Ethiopia

በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የስዊድን ኤምባሲ አምባሳደር የሆኑት ቱርብያን ፐተርሾን ወጣቶችን በሥነ ጥበብ ፈጠራ ዘርፍ ዉስጥ ማሰማራት ባህል እንዲለማ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ። አምባሳደሩ የባሕል እድገት ለማህበራዊ ለዉጥና ለዲሞክራሲ ስረዓት ግንባታ አስተዋህፆ እንዳለዉም አክለው አመልክተዋል።

በዚህ በሶስት ዓመት ዉስጥ ከ2000 በላይ ወጣቶች በፕሮጄክቱ እንደምሳተፉና የነሱ የሥራ ዉጤት ደግሞ ከሚሊዮኖች ጆሮና ዓይን እንደምደርስ አቶ ተሾመ ይገምታሉ።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ