1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ የቀጠለዉ የሠራተኞች ተቃዉሞ

ዓርብ፣ ግንቦት 19 2008

የፈረንሳይ መንግሥት የሥራ ሰዓት እና ክፍያን አስመልክቶ ለማሻሻል ያቀረበዉ የሠራተኞች የሥራ ሁኔታ ረቂቅ ደንብ በሀገሪቱ የቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የነዳጅ ማጣሪያ ሠራተኞች የጀመሩት ተቃዉሞ ፈጥሮት የነበረዉ የነዳጅ እጥረት መንግሥት ከብሔራዊ ክምችቱ ወጪ በማድረጉ በመጠኑ እንደቀነሰ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1IvOf
Frankreich Proteste Paris
ምስል picture-alliance/epa/G. Horcajuelo

[No title]

ያም ሆኖ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያለዉ የሀገሪቱ የሠራተኞች ማኅበር በመላዉ ሀገሪቱ የጠራዉ ተቃዉሞ የማርሴል አዉሮፕላን ማረፊያን እንቅስቃሴ አስተጓጉሏል። የተቃዉሞ ጥሪዉ እና እንቅስቃሴዉ ቢስፋፋም የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትራቸዉ ማኑዌል ቫልስ መንግሥት ሊያሻሽል ባቀረበዉ የሠራተኞች የሥራ ሁኔታ ማሻሻያ ረቂቅ እንደሚገፋበት ነዉ ዛሬ ይፋ ያደረጉት። ስለፈረንሳይ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ፓሪስ የምትገኘዉን ዘጋቢያችን በስልክ ጠይቀናታል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ